
የባልደራስ ሊቀመንበር አቶ እስክንድር ነጋ የፍርድ ቤት ውሎ ዘገባ ( ረቡዕ ሃምሌ 22 ቀን 2012 ዓ.ም) "የምዳኘው በህዝብ ህሊና ነው" እስክንድር ነጋ!!
እስክንድር ነጋ ዛሬ ሐምሌ 22/2012 በፌደራሉ የመጀመሪያ ደረጃ ፍርድ ቤት አራዳ ምድብ ተረኛ ችሎት መቅረቡ ታውቅዋል።
የፍ/ቤት ውሎው ጠቅለል ሲል:-
* አዲስ አበባ ላይ ለተፈጠረው ሁከትና ብጥብጥ ጠርጥርነዋል
* የምስክር ቃሎች እየተቀበልን ነው...
*የእጅ ስልካቸውን እያስመረመርን ነው ...ውጤቱ በመጠባበቅ ላይ ነን...
* ለ14 ሰው የህይወት መጥፋት ...
የአስክሬን ምርመራ ውጤት ለጳውሎስ ሆስፒታል ፅፈን መልስ እየጠበቅን ነው...
* 54 ሚሊዮን ብር ለሚገመት ንብረት ውድመት... የሚሉና በባለፈው ቀጠሮ ላይ የተነሱ ተመሳሳይ ክሶች በዚህም ችሎት ተነስተዋል። የአቶ እስክንድር ጠበቆች በበኩላቸው ፖሊስ ደንበኛቸውን ሆን ብሎ እያጉላላ በመሆኑ የዋስትና መብት እንዲጠበቅላቸው ጥያቄ ያቀረቡ ቢሆንም ችሎቱ ለነሃሴ 1/2012 ተጨማሪ የግዜ ቀጠሮ ሰጥትዋል።
ዛሬ በዋለው ችሎት ላይ አቶ እስክንድር ለፍ/ቤት መናገር የሚፈልገው ካለ ጠይቆ የነበረ ሲሆን፣ እስክንድርም "ክሱ ለእኔ ሁለተኛ ነገር ነው። ነገር ግን ወደ ችሎት ስንገባ ሁልግዜ የመንግስት ሚዲያዎች እንዲገቡ ይፈቀዳል። ነፃ ሚዲያ ይከለከላል ...ለምን?... እኔ የምዳኘው በሰው ህሊና ነው። በህዝቡ ህሊና ነው። የመንግስት ሚዲያ ብቻ ሳይሆን ነፃ ሚዲያም እንዲገቡ" ሲል ሃሳብ አንስትዋል። ችሎቱም ከሚቀጥለው ቀጠሮ ጀምሮ ለነፃ ሚዲያ ክፍት መሆኑንና በር ላይ ክልከላ እንዳይደረግባቸው አዝዋል።