Ethiopia : TPLF/Tigray "ጦርነቱ አሳፋሪ ብቻ ሳይሆን፣ አላማ የለሽ ነው" ( General Birhanu Jula )

Просмотров: 74   |   Загружено: 5 год.
icon
Hagere Media
icon
8
icon
Скачать
iconПодробнее о видео
ጦርነቱ አሳፋሪ ብቻሳይሆን፣ አላማ የለሽ ነው !
የመከላከያ ሠራዊት ሕዝብ እንዳይጎዳ የህወሓት ጽንፈኛ ኃይልን ለይቶ ለመምታት በጥንቃቄ እየተንቀሳቀሰ መሆኑን ጄኔራል ብርሃኑ ጁላ አስታወቁ
ምክትል ኤታማዦር ሹም እና የኦፕሬሽን ዘርፍ ሓላፊ ጄኔራል ብርሃኑ ጁላ በሰጡት መግለጫ፣ ማክሰኞ ከምሽቱ 4:00 ላይ ትግራይ ክልል በሚገኘው የሰሜን ዕዝ ላይ የራሳችን መንግሥት አካል በሆነው በጽንፈኛ የሕወሓት ኃይል ጥቃት ደርሶበታል ብለዋል።
መከላከያ ይህን መሰል ጥቃት ይፈጸማል የሚል ግምት አልነበረውም ያሉት ጄነራሉ ፣ የሠራዊቱ ተልዕኮ ሕገ መንግሥቱ ከሚፈቅደው ውጭ የሚንቀሳቀስ ኃይል ላይ እርምጃ መውሰድ እንደነበር አስታውስዋል።
በዚህ ጊዜ ከወገኑ ይህ ጥቃት ይመጣል ብሎ ያላሰበው ሠራዊቱ በፅንፈኛው ሕወሓት ቡድን ጥቃት ደርሶበታል ብለዋል።
የትግራይ ሕዝብ ይህንን ጥቃት አልቀበልም ብሎ ከመከላከያ ሠራዊቱ እና ከመንግሥት ጎን መሆኑን ጀነራል ብርሃኑ ተናግረዋል።
ጥቃት ለደረሰበት ለመከላከያ ሠራዊታችን ድጋፍ የሚሰጥ ኃይል ወደ ቦታው መንቀሳቀሱን የጠቀሱት ጄነራል ብርሃኑ ጁላ፣ እንዲዋጋ ተልእኮ የተሰጠው ኃይል ወደ ጦርነት እንዲገባ ተገዷል ብለዋል።
ሠራዊቱ አርሶአደሩን ሰብል በመሰብሰብ እና አንበጣን በመከላከል ድጋፍ እያደረገ ባለበት ወቅት የህወሓት ጽንፈኛ ኃይል ጦርነት መክፈቱ ለሕዝብ ደንታ የሌለው መሆኑን እንደሚያሳይ ጄነራሉ ገልጸዋል።
“በአሁኑ ወቅት የተጎዱት ከሁሉም ወገን ህክምና እያገኙ ነው፤ አንዳንዶቹም እያመለጡ ወደ ሠራዊታችን እየገቡ ነው” ሲሉ በመግለጫቸው ላይ ተናግረዋል።
“አገራችን ያላሰበችው፣ ዓላማ የሌለው ጦርነት ውስጥ ገብታለች፤የትግራይ ወጣት በዚህ ዓላማ ቢስ ጦርነት ውስጥ መግባት የለበትም፤ ኢትዮጵያ ስትኖር የትኛውም አካባቢ ተንቀሳቅሶ መሥራት፣ ማደግ ይችላል”ሲሉ ተደምጠዋል።
የመከላከያ ኃይሉ ሕዝብ እንዳይጎዳ ለማድረግ ሕዝብ እና ጽንፈኛ ኃይሉን ለይቶ ለመምታት በጥንቃቄ እየተንቀሳቀሰ መሆኑን ተናግረዋል።
#EthiopianNews
#Tigray
#ethiopianentertainment @HagereMedia ​#Hageremedia #birihanujula

Похожие видео

Добавлено: 56 год.
Добавил:
  © 2019-2021
  Ethiopia : TPLF/Tigray 'ጦርነቱ አሳፋሪ ብቻ ሳይሆን፣ አላማ የለሽ ነው' ( General Birhanu Jula ) - RusLar.Me