
ብፁዕ አቡነ ሉቃስ ቅዱስ ፓትርያርክ አቡነ መርቆርዮስን እስከ መጨረሻው ተከትለው በስደት ብዙ ዘመን አብረው የገፉ፣ የተገፉ ናቸው። አቡነ ሉቃስ በጅምላ የተጨፈጨፉ እና በየዱሩ ወድቀው የቀሩትን የማይካድራ ሰማእታትን በክብር እንዲቀበሩ አድርገው በቦታው ተገኝተው ፍትሃት ያደረጉ ብቸኛ ሊቀ ጳጳስ ናቸው። ለብዙ ወራት ደግሞ እጅግ ብዙ ገዳማትን በእግር ጭምር በመላ ኢትዮጵያ እና ኤርትራ ውስጥ ያለውን ታላቁን ደብረ ቢዘን ገዳም ጎብኝተው ድጋፍም አዳርሰዋል።
ብፁዕ አቡነ ሉቃስ 🗣
"…ተው ቤተ ክርስቲያንን ስማት። እህል አታቃጥል፣ ህፃናትን አትግደል፣ ሽማግሌዎችን አክብር። ወንድ ከሆንክ ደግሞ ወንድ ለወንድ በዚያ በተራራው ላይ ተዋጋ። መንደር ለመንደር ለምን ታውደለድላለህ…? እንዴ…! የጀግና መፈታተኛው እኮ ከተማ ላይ አይደለም። መንደር ለመንደር አይደለም ወጣ ብሎ ነው ትግሉ። ሜዳ መርጦ የጀግና እኮ መዋጊያ አለው ቦታ አለው እኮ። ዝም ብለህ የፈሪ ዱላ… በገዛ ወርቃችን፣ በገዛ ብራችን ድሮን ገዝተህ አገር ታጠፋለህ…? ኧረ ልብ ይስጥህ። ልብ ይስጥህ ትልሃለች ቤተ ክርስቲያን። ዛሬ የቆምኩት ሽማግሌ ነገ መሬት ስገባ አታገኘኝም እኔን።
ማን ይመሰክርልሃል…?
ማን ይናገርልሃል ታሪክህን?
እኛን ለማጥፋት ትተጋለህ ነገርግን አታገኘንም!"
#ethiopianorthodoxtewahedochurch #ethiopianews #ethiopianorthodoxchurch #ethiopianorthodoxsibket #ethiopianorthodoxtewahdo #ethiopian #ethiopia #ethiopiannews
#ስብከት @HagereMedia #Hageremedia