
"ድል አለ በስምህ"
ድል አለ በስምሀ ድል አለ በቃልህ/2/
ተራራው ይናዳል አማኑኤል ስልህ
ባህር ይከፈላል መድሐኔዓለም ስልህ
አዝ....
ቃዴስን ታላቁን በረሃ
አለፍነው ሳንጠማ ውሃ
ፈርኦንን ከባህር የጣለው
ጌታዬ የፀና ስምህ ነው
አምላኬ የፀና ሰምህ ነው
አዝ........
በእልልታ ቢፈርስ ኢያሪኮ
ጠላትም ቢወድቅ ተማርኮ
ቢሰጠን ለኛ ከተማው
የሆነው ሁሉ ካንተ ነው/2/
አዝ.............
ከጥፋት ጥልቁ ብናመልጥ
የፋራ ውሃ ቢጣፍጥ
ብንበላ መና ከሰማይ
ስለሆንክ ነው አዶናይ
ሰለሆንክ ነው ሁሉን ቻይ
አዝ..................
የቆምነው ዛሬ በሕይወት
ስምህን አርገን ነው ጉልበት
ከሜዳ ተጠርተን ብንነግስ
ሆነህ ነው ክብርና ሞገስ/2/
አዝ..........................
ድል አለ በስምሀ ድል አለ በቃልህ/2/
ተራራው ይናዳል አማኑኤል ስልህ
ባህር ይከፈላል መድሐኔዓለም ስልህ