
#Yemane_Nigus
መምህር የማነ ንጉስ ይባላል። በትግራይ እንደርታ ነው የተወለደው። ከመቀሌ ዩኒቨርስቲ በታሪክ ትምህርት ተመርቆ በዚሁ ትምህርት ሲያስተምር ነበር። 2007 ዓ.ም በተካሄደው ምርጫ የአረና ፓርቲ ዕጩ ሆኖ በመቅረቡ ተከሶ 3 ዓመት ተፈርዶበታል። ፍርዱንም በመቃወሙ በችሎት መድፈር 6 ወር ተጨምሮለት ከ2007-2010 ዓ.ስ 3 ዓመት ከ 6 ወር በመቀሌ ማረሚያ ቤት በእስር አሳልፏል። የማነ ትግራይ ውስጥ ሕወሃትን ከስልጣን ለማባረር በቅርቡ የተቀሰቀሰውን ሕዝባዊ አመጽ ከሚመሩት ታጋዮች አንዱ ነው።