
*****************************************
በመከላከያ ሰራዊት፣ በአማራ እና አፋር ልዪ ሃይል፣ እንዲሁም በፋኖ እና በአማራ ሚሊሻ የተደቆሰው የወያኔ ሕወሃት ስርዓተ ቀብር የደቡብ አውስትራሊያ ዋና ከተማ በሆነችው አድላይድ ከተማ ተከናውኗል። እድር ልፈፋ
አቤት ! አቤት ! አቤት ! ነው የሚባለው መቼም ! … መቼስ እኛ ጥሎብን በሕይወት ዘመኑ አንድም በጎ ተግባር አከናውኖ የማያውቀው ፍጡር፣ ወደ መቃብሩ ሲወርድ ያለስሙ ስም ሰጥተን፣ ባልሰራው ስራ አሞካሽተን፣ አልፎ ተርፎም ለሙሾ ደርዳሪ፣ አስለቃሽ ገንዘብ ከፍለን፣ ደረት ደልቀን፣ መሸኘት ነበር ልምዳችን።
ትናንት በአድላይድ ያከናወነው የሕወሃት የቀብር ስነ ስርዓት ግን ከዚህ በእጅጉ የተለየ ነበር !
አዎን! አሁን እንኳን ማቆም እያስቸገረ ላለው፣ በሚልዮን ለሚቆጠሩ ኢትዮጵያውያን ሞት፣ አካል መጉደል፣ እስራትና ስቃይ፣ መፈናቀልና አገር ጥሎ መሰደድ፣ ምክኒያት የሆነው ሕወሃትን በደስታ! በዕልልታ! ሆ ! እያልን ! በአንድነት እየጨፈርን! ግብዓተ-መሬቱን ላፋጠነው ለጀግናው የመከላከያ ሰራዊታችን፣ ለአማራና የአፋር ልዩ ሃይል አንበሶች፣ እንዲሁም ለፋኖና የአማራ ሚሊሻ የሚገባቸውን ክብርና ምስጋና እየቸርን ፣ ቀደም ሲልም ሆነ አሁን የሕወሃትን አገዛዝ ከሕዝባችን ጫንቃ ላይ ለማውረድ፣ አኩሪ መስዋዕትነት ከፍለው ያለፉ ጀግኖችን እያሰብን፣ ባልጠበቀው መልኩ በተለይም በአማራ ልዪ ሃይልና ፋኖ በደረሰበት ሽንፈት፣ የውርደት ጽዋውን ጨልጦ እንደ ደነበረ ጅብ ቅዘኑን እያንበጫበጨና ፈሱን እያንዛረጠ ከመፈርጠጡ በፊት ማይካድራ ላይ ለጨፈጨፋቸው ንፁሃን ወገኖቻችን፣ እንዲሁም በአሰቃቂ ሁናቴ ለተገደሉት የሰሜን ዕዝ የመከላከያ ሰራዊታችን የሕሊና ፀሎት እያደረስን፣ ልዩ በሆነ መልኩ አከናውነናል።
ሙሉ ፕሮግራሙን በዝርዝር እስካቀርበው ይቺን ቪድዪ ላካፍላችሁ !
Ethiopia | Ethiopian News | Abiy Ahmed | TPLF| Debretsion Gebremichael | Zehabesha News | Ethio Forum | Andafta | Seyoum Teshome | Eritrea News | Ethio Forum | Abel Birhanu | Seifu on EBS | Getachew Reda | Ethio 360 | Esat News | ሰበር ዜና | መረጃ | አብይ አህመድ | ህወሃት | Joe Binden | Trump | Isaias Afewerki@HagereMedia #Hageremedia