Ethiopia : “የቦሌ አበባዎች ” እና ዶ/ር አብይ አሕመድ - ከሰው ነፍስ ይልቅ፣ የአበባ መቀጠፍ የሚያሳስባቸው የኢትዮጵያ መሪ

Просмотров: 117   |   Загружено: 5 год.
icon
Hagere Media
icon
6
icon
Скачать
iconПодробнее о видео
ይድረስ ..ለማይደርስልን መንግስት
************************
እንደምነህ መንግስት እኛ አለን በደህና
ባመቻቸህልን የለውጥ ጎዳና
ሺዎችን ገብረን ፣ ለአንድ ብልፅግና
እየተሰበርን ሰበር በሚል ዜና
ተራ እየጠበቅን ፣ ለሞት ተሰልፈን
እግረ መንገዳችን ፣ ድንገት ከሞት ተርፈን
ከደብዳቢ ጋራ
ደብዳቤ እስክንልክ፣ በደማችን ፅፈን
እኛ አለን በተድላ
እንደምነህልን?
እንደምነህልን ካልንህስ በኋላ?!
እኛ አለን በድሎት
እኛ አለን በፀሎት
ከገዳያችን ጋር ፣ ቀብር ስናስፈጥም
ስንኖር ኢትዮጵያዊ
ስንሞት ምን እንደሆንን ፣ ባናረጋግጥም
እኛ አለን በተአምር ፣ እኛ አለን በደህና
እየተገደልን
"መግደል መሸነፍ ነው" ፣ በሚል ፍልስፍና!
አንተ ግን እንዴት ነህ?
እልፎች ሚቃወሙህ ፣ የብዙዎች ምርጫ
ፍትህ ለሚጠይቅ ፣ የምትሰጥ መግለጫ
የእልፎች አሻጋሪ ፣ የእልፎች እንቅፋት
ትኩረት የምትሰጥ
ከሰዎች ነፍስ ይልቅ ፣ ለአበቦች መጥፋት
እንደምነህ አንተ?!"
#Ethiopia
#AbiyAhmed
#Belay_Bekele_Weya @HagereMedia ​#Hageremedia

Похожие видео

Добавлено: 56 год.
Добавил:
  © 2019-2021
  Ethiopia : “የቦሌ አበባዎች ” እና ዶ/ር አብይ አሕመድ - ከሰው ነፍስ ይልቅ፣ የአበባ መቀጠፍ የሚያሳስባቸው የኢትዮጵያ መሪ - RusLar.Me