Hangaasa Ahmed Ibraahim : "ሽመልስ አብዲሳ ተጠያቂ ሊሆን ይገባል" ዶ/ር ሃንጋሳ #abiyahmed #oromia #Hangaasa

Просмотров: 394   |   Загружено: 3 год.
icon
Hagere Media
icon
9
icon
Скачать
iconПодробнее о видео
ሰበር መረጃ "አጃቢዬን ዛሬ ገድለዉብኛል ነገ እኔንም ቢገሉኝ እውነትን ከመናገር አላቆምም"
=====
የፓርላማው አባል ዶክተር አንጋሳ ኢብራሂም ያልተጠበቀ ጠንካራ መልዕክት አስተላለፉ
የኦሮምያን መንግስት አጋለጡ!!

በኦሮምያ ዉስጥ ግድያ የሚፈጸመው በኦሮምያ ፕሬዝደንት ጽፈት ቤት እና በኦሮምያ ብልጽግና ቢሮ አማካኝነት ነው ሲሉ ተናገሩ
የፓርላማ አባሉ በማህበራዊ ሚድያ የቀጥታ ስርጭት ቀርበው በቁጣ እና በእልህ ባስተላለፉት መልእክት በኦሮምያ እየተገደሉ ያሉት የወሎ ሙስሊሞች ተመርጠው ነው ይህንን የአማራም ብልጽግና ያውቃሉ ሲሉ ተደምጠዋል፡፡
በተጨማሪም ከተናገሯቸው ሃሳቦች መሃል
ሁለት አይነት ሸኔ ነው ያለው ትክክለኛው ሸኔ አይጨፈጭፍም፣ እየጨፈጨፈ ያለው የኦሮሚያ ብልጽግና የሚመራው ነው
ሽመልስ አብዲሳን ጨምሮ የክልሉን ባለስልጣናት በማሰር አብዲ ኢሌ ሲታሰር ሶማሊያ ሰላም እንደሆነው ሁሉ በኦሮምያም ሰላም ይስፈን
ዶ/ር አብይ የኦሮሚያ ክልልን ካቢኔን አፍርሰህ በአዲስ ቀይረው ይህንን ካላደረክ አማራ እንዲጨፈጨፍ የምታደርገው አንተው ነህ የሚል ድምዳሜ እወስዳለሁ
እኔ ብሞት እንኳን ወንድሞቼ ብሄር ብሄረሰቦች እውነቱን ስሙ
ዶ/ር አብይ መሬት ላይ ወርደህ ህዝቡን ይቅርታ ጠይቅ፣ አንተን እና ህዝቡን ለይተው ሊበሉህ ደጅህ ላይ የቆሙ ጅቦች አሉና ቅደማቸው
አጃቢዬን ዛሬ ገድለዉብኛል ነገ እኔንም ቢገሉኝ እውነትን ከመናገር አላቆምም
ኦነግ ለዘመናት ወለጋ ውስጥ ነበር፣ ኦነግ የመግደያ፣ የመጨፍጨፊያ አቅሙን ከየት አመጣው? አቅሙን ያገኘው ከክልሉ መንግስት ነው
እነ ሽመልስ ዙሪያውን ከበው ሊበሉህ ነው፣ የመጨረሻው ሰዓት ላይ ደርሰሃል አይንህን ግለጥ
አማራን ኦሮሚያ ውስጥ መጨፍጨፍ የሚጎዳው ከአማራ ይልቅ ኦሮሞን ነው፣
አጉል ጥጋብ እና ሁኔታ ውስጥ ገብታችሁ የአማራን መገደል የምትደግፉ የኦሮሞ ወንድሞቼ እረፉ (ዋ እረፉ ብያለሁ)፣ ነገ ጠዋት አማራ ኦሮሞ ላይ እንዲነሳና እርስ በእርስ እንድንትላለቅ ነው ፍላጎቱ፣ የኦሮሞ ወንድሞቼ ንቁ (በጭራሽ በኦሮሞ ብልጽግና ገመድ እንዳትጠለፉ)
ኦሮሚያ የሁላችንም ቤት ነው፣ አማራው ተመርጦ ሲታረድ ለምን ካላልን ነገ መከራው በኛና በልጆቻችን ላይ ይደርሳል
ዶ/ር አብይ እስኪ ድንገት ማንንም ሳትነግር በሂሊኮፕተር በረህ ጅማ፣ አርሲ፣ሀረርጌ፣ ወለጋ፣ ባሌ ሂድና ህዝቡን ችግራችሁ ምንድነው በላቸው - የሚመር ዜና ያሰሙሃል
የሚሉ ይገኙበታል፡፡ የፓርላማው አባል ዶክተር ሃንጋሳ በንግራቸው መጨረሻ ፓርቲያቸው ብልጽግናንና መሪያቸው ዶክተር አብይን እንደሚወዱ የተናገሩ ሲሆን አቶ ጁሃር መሃመድንም ይቅርታ ጠይቀዋል፡፡
#Hangassa #ethiopia #abiyahmed #ethio360 #ethiopian #Wollega #amharaunderattack #AmaraGenocide #amhara #oromiya

Похожие видео

Добавлено: 56 год.
Добавил:
  © 2019-2021
  Hangaasa Ahmed Ibraahim : 'ሽመልስ አብዲሳ ተጠያቂ ሊሆን ይገባል' ዶ/ር ሃንጋሳ #abiyahmed #oromia #Hangaasa - RusLar.Me